ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳትፎውን አጠናክሮ ቀጥሏል
የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ከሚያከናውነው የመንገድ መሠረተ ልማት ግንባታና ጥገና ስራዎች ጎን ለጎን በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መስኮች ላይ በመሳተፍ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባሳለፍነው ሳምንት በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አባይ ምንጭ ት/ቤት አካባቢ የአቅመ ደካማ ቤት እድሳት ስራ በይፋ ጀምሯል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አብረውት የሚሰሩ ማህበራትን በማስተባበር የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት ስራውን የሚከናወን ሲሆን፣ አጠቃላይ የእድሳት ስራውን ከአንድ ወር ባነስ ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለተጠቃሚዎች የሚተላለፍ ይሆናል።
በቤት እድሳት ማስጀመሪያ ስነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 1 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጀ ፈይሳ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚያከናውናቸው ተግባራት በአርዓያነት የሚታዩ መሆናቸውን ጠቅሰው ሌሎች ተቋማትም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሣትፏቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity