+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ዓለም አቀፍ የስማርት ሲቲ ስታንዳርድን ያሟሉ አዳዲስ የመንገድ ኮሪደሮች ሊገነቡ ነው

አዲስ አበባ፣የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ የስማርት ሲቲ ስታንዳርድን ያሟሉ አዳዲስ የመንገድ ኮሪደሮች ሊገነቡ እንደሆነ አስታውቋል፡፡

ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት አራት የሚለሙት የመንገድ ኮሪደሮች ተለይተዋል፡፡

በዚህ መሠረት የሚለሙት የመንገድ ኮሪደሮች የሚከተሉት ይሆናሉ:-

– ከ #አራት_ኪሎ በ#መስቀል_አደባባይ እስከ #ቦሌ_ድልድይ (7 ኪ.ሜትር)

– ከ #ቦሌ_አየር_መንገድ እስከ #መገናኛ_ዲያስፖራ_አደባባይ (4.9 ኪ.ሜትር)

– ከ #መገናኛ_ዲያስፖራ_አደባባይ#አራት_ኪሎ በኩል የ #አድዋ_ድል_መታሰቢያ አካባቢ ድረስ (6.4 ኪ.ሜትር)

– ከ #ፒያሳ_አድዋ_ድል_መታሰቢያ ዙርያ፣ በ #ለገሃር_ሜክሲኮ፣ በ #ሳርቤት በኩል እስከ # ወሎሰፈር (10 ኪ.ሜትር) ናቸው ተብሏል።

እነዚህ የመንገድ ኮሪደር ልማቶች ሁለንተናዊ የመንገድ ዘመናዊነት ያሟሉ ከመሆናቸውም በላይ ዓለም አቀፍ የስማርት ሲቲ ስታንዳርድን በማሟላት የከተማችንን ደረጃ የሚለውጡ ይሆናል።

የመንገድ ኮሪደር ፕሮጀክቶቹ አዋሳኝ የወንዝ ተፋሰሶችን ያቀፉ፣ የሳይክልና ሞተር አልባ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ፣ የከተማዋን ማስተር ፕላን እና አርባን ዲዛይን ታሳቢ ያደረጉ እንዲሁም ለከተማዋ ዘመናዊ የትራንስፖርት ፍሰት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ መሆናቸው ተመላክቷል።

በተጨማሪም አስፈላጊ በሆኑ የኮሪደሩ ቦታዎች ላይ ስታንዳርዳቸውን የጠበቁ ተሸጋጋሪ ድልድዮች፣ ማሳለጫዎች እና ሰፋፊ መጋቢ መንገዶችን እና የከተማ አረንጓዴ ልማትን ያካተተ እንደሚሆንም ታውቋል።

የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔም 3ኛ ዓመት 8ኛ መደበኛ ስብሰባው የቀረበውን የመንገድ ኮሪደር ልማት እቅድ በጥልቀት መርምሮ በሙሉ ድምፅ በማፅደቅ ወደ ስራ እንዲገባና ልዩ ክትትል እንዲደረግ መወሰኑን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል ።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.