“ከእዳ ወደ ምንዳ” በሚል ርእስ የሠራተኞች ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ አመራርና ሰራተኞች “ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ የመወያያ ሰነዶች ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ ማብራሪያ የሰጡት ሬጉራቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ታከለ ሉለና እንደገለፁት፤ ከትርክት ጋር በተያያዘ የሚታዩ የአስተሳሰብ ልዩነቶችን ወደ ጎን በመተው፣ ገዢ የሆኑ ትርክቶችን በመረዳት እንደ ሀገር አንድ በሚያደርጉን የወል ትርክቶች ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም በተለያዩ አካባቢዎች ለሠላም እጦት ምክንያት የሆኑ ልዩነቶች ከግጭት ይልቅ በውይይት በሚፈቱባቸው ሁኔታዎች ላይ በማተኮር የሀገር ሉአላዊነትን ማስከበር እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ሁሉም የባለስልጣኑ ሰራተኛ እና አመራሮች በሚኖርበት አካባቢ የሰላም ሠራዊት በመሆንና በሥራ ቦታቸው የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል የመንገድ መሰረተ ልማት ለሁሉም የከተማዋ የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ የተጀመረውን ስራ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ኢንጅነር ታከለ አያይዘው ገልፀዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የገዢ ትርክት ግንባታ፣ የአገልግሎት አሠጣጥ፣ የሀገር ሀብት አጠቃቀምና የሀገር ሰላም በሚሉ የመወያያ አጀንዳዎች ላይ የባለስልጣኑ አመራሮችና ሰራተኞች በተለያዩ የውይይት መድረኮች ላይ ሰፊ ውይይት አካሂደዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity