+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የቃሊቲ – ቂሊንጦ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት መሠረታዊ እውነታዎች

አጠቃላይ 10.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን በ50 ሜትር የጎን ስፋት እየተገነባ ይገኛል።

• 5 ድልድዮችን አካቶ እየተገነባ የሚገኝ የመንገድ ግንባታ ስራ ነው።

ከእነዚህ ውስጥ ሁለቱ ወንዝ ተሻጋሪ ድልድዮች ሲሆኑ ሶስቱ ደግሞ መንገድ ተሻጋሪ ድልድዮች ናቸው።

• የመጀመሪያው ድልድይ በቡልቡላ ወንዝ ላይ የተገነባው እና 175 ሜትር ርዝመት እና በግራና በቀኝ መተላለፊያው በኩል 34 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ነው።

• የቡልቡላ ወንዝን አቋርጦ የሚያልፈው ይህ ድልድይ ከታች ወደ ላይ 30 ሜትር የሚረዝም ከፍታም አለው፡፡

• ሁለተኛው ወንዝ ተሻጋሪ ድልድይ በትልቁ የአቃቂ ወንዝ ላይ የተገነባው ሲሆን 325 ሜትር ርዝመት አለው።

• የትልቁ አቃቂ ወንዝ ድልድይ 42 ሜትር ከፍታ ያለው ሲሆን፣ እያንዳንዱ የድልድዩ ምሰሶ ከመሬት በታች እስከ 30 ሜትር በሚደርስ ጥልቀት መሠረት የተገነባ ነው፡፡

ቀሪዎቹ 3 የመንገድ ተሻጋሪ ድልድዮች ደግሞ በፕሮጀክቱ የተለያየ ስፍራዎች ላይ የተገነቡ ሲሆን፣ቅሊንጦ አካባቢ በሚገኘው ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በሚገኙት መንገዶች በላይ ተሻግረው የሚያልፉ እና ወደ ውጨኛው የቀለበት መንገድ ጋር የሚያሻግሩ ናቸው፡፡

የፕሮጀክቱ የግንባታ ውል ዋጋ 2.3 ቢሊዮን ብር ሲሆን፣ የቻይና ኮንስትራክሽን ኮሙኒኬሽን ካምፓኒ የግንባታ ሥራውን እያከናወነው ይገኛል።

የፕሮጀክቱ አማካሪ ድርጅት ሀይ ዌይ ኢንጂነርስ እና ኮንሰልታንት ሲሆን፣ አሁን ላይ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ አፈፃፀም 92 በመቶ ደርሷል።

የቃሊቲ – ቂሊንጦ መንገድ ፕሮጀክት የውስጠኛውን ቀለበት መንገድ ከውጩ ጋር በቀጥታ በማስተሳሰር በአካባቢው ቀልጣፋ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር ከማስቻሉም በተጨማሪ በኮዬ ፈቼ እና አካባቢው ባሉ የጋራ መኖሪያ መንደሮችና በዙሪያው ያሉ ነዋሪዎች በአቋራጭ ወደ መሃል ከተማ እንዲጓጓዙ የሚያስችል ሌላው የደቡብ አዲስ አበባ ክፍል አዲስ የመንገድ ኔትወርክ አካል ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.