+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በ9ኛው የኢትዮጵያ የከተሞች ፎረም ላይ የአዲስ አበባ ከተማን ገፅታ የሚያሳዩ የተለያዩ የልማት ስራዎች ለእይታ ቀርበዋል

የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ከየካቲት 9 – 15 ቀን 2016 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ በተዘጋጀው የኢትዮጵያ የከተሞች ፎረም ላይ እየተሳተፈች የምትገኘው የአዲስ አበባ ስኬታማ ተሞክሮዎችቿን እያካፈለች ትገኛለች።

በኤግዚቢሽኑ ላይ የቀረቡ ልዩ ልዩ የመሠረተ-ልማት ፊዚካል ሞዴሎች፣ አጫጭር የዘጋቢ ፊልም ቅንብሮችና የተለያዩ የፈጠራ ውጤቶች የጎብኚዎችን ቀልብ ስበዋል።

ከወትሮው በተለየ ዝግጅት በዘንድሮው የከተሞች ፎረም ላይ እየቀረበ ያለው የመዲናዋ ኤግዚቢሽን የቨርቹዋል ሪያሊቲ እይታን አካቶ የቀረበ ነው።

በኤግዚቢሽኑ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኢያሱ ሰሎሞን እንደገለፁት በኤግዚብሽኑ ላይ ከቀረቡ ይዘቶች መካከል በመንገድ መሰረተ- ልማት ዘርፍ የተከናወኑ እና የሚከናወኑ ስራዎች ይገኙበታል።

በተለይም ሁሉንም ትራፊክ ታሳቢ ባደረገ መልኩ ከቦሌ ወደ መገናኛ ሊሰራ የታቀደውን አካታች የመንገድ ማሻሻያ ፕሮጀክት የሚያሳዩ ፊዚካል ሞዴሎች የጎብኚዎችን ቀልብ መሳባቸውን አቶ ኢያሱ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

አምስተኛ ቀኑን በያዘው በ9ኛው የኢትዮጵያ የከተሞች ፎረም ኤግዚቢሽን ላይ አዲስ አበባ ከተማ በከተማ ፕላን፣ በመንገድ፣ ቤቶች ልማት፣ በውሃና ፍሳሽ፣ በዲዛይንና ኮንስትራክሽ፣ በሜጋ ፕሮጀክቶች፣ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን፣ በመሬት ልማት፣ በህብረተሰቡ ተሳትፎ፣ በምገባ፣ በባህልና ቱርዝም ዘርፎች የተለያዩ ተሞክሮዎችን የሚያሳዩ የኤግዚብሽን ይዘቶች ለእይታ ቀርበዋል።

በማኑፋክቸሪንግ እና ሥራ ክህሎት መስኮች የተሰማሩ የዘርፉ አንቀሳቃሾች ያቀረቧቸው የፈጠራ ውጤቶችም ለኤግዚቢሽኑ ተጨማሪ ድምቀት ማላበሳቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.