በጀርመን አደባባይ የመንገድ ማሻሻያ ስራ የመጀመሪያ ደረጃ የአስፋልት ማንጠፍ ስራ ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 12 ቀን 2016 ዓ.ም፤ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በጀርመን አደባባይ እያካሄደ በሚገኘው የመንገድ ማሻሻያ ስራ የመጀመሪያ ደረጃ የአስፋልት ማንጠፍ ስራ ተጠናቋል፡፡
ቀደም ሲል በለቡ የመንገድ መጋጠሚያ አካባቢ ይታይ የነበረውን የትራፊክ መጨናነቅ ችግር ለመፍታት በተካሄደው የማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድይ ግንባታ የትራፊክ ፍሰቱ የተሻሻለ ቢሆንም፤ በጀርመን አደባባይ ላይ የትራፊክ ጫና ይከሰት እንደነበር ይታወሳል።
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በዚህ ሥፍራ የሚታየውን የትራፊክ ፍስት የተቀላጠፈ ለማድረግ አደባባዩን የማንሳትና በትራፊክ መብራት የመተካት ሥራ እያካሄደ ይገኛል፡፡
የትራፊክ ፍሰት ማሻሻያ ስራው የትራፊክ እንቅስቃሴ በማይበዛባቸው የምሽት ክፍለ ጊዜና የዕረፍት ቀናትን በመጠቀም እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን አሁን ላይ የመጀመሪያ የአስፋልት ማንጠፍ ስራው ተጠናቋል፡፡
ቀሪ የማጠቃለያ ስራዎችን እና የትራፊክ መብራት ተከላውን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል።
የአደባባይ ማሻሻያ ስራው መከናወኑ በአካባቢው ያለውን ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰትና ጫና በአግባቡና በፍጥነት ለማስተናገድ እንደሚያስችል ይታመናል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity