+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ባለስልጣኑ 37ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የተሳካ እንዲሆን መንገዶችን የማስዋብ ስራ አጠናቋል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን 37ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 44ኛው የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ በስኬት እንዲጠናቀቅ ለማድረግ የመንገዶች ጥገና እና የማስዋብ ስራዎችን አከናውኗል፡፡

ባለስልጣኑ የከተማዋን ገፅታ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ለሚመጡ እንግዶች ለማስታዋወቅና በምሽት ወቅት የሚኖራቸውን እንቅስቃሴ ለማሳለጥ የመንገድ መብራቶችን የማሻሻልና የማዘመን ስራ አጠናቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በመንገድ አካፋዮች ውስጥ የተተከሉ ልዩ ልዩ ዛፎችን በጌጣጌጥ መብራቶች የማስዋብና የእግረኛ መንገዶችንም የማሻሻል ስራዎችን አጠናቋል፡፡

ባለስልጣኑ በተለይም ከቦሌ ዓለም ዓቀፍ አውሮፕላን – በመስቀል አደባባይ – አራት ኪሎ ቤተመንግስት ፣ ከካሳንችስ – ቤሄራዊ- ሜክሲኮ – የህብረቱ ዋና ፅ/ቤት ድረስ ባለው መንገድ ላይ የፖቶል ጥገና የከርቭስቶን ቀለም ቅብ ፣ የድሬኔጅ መስመር ፅዳት ፣የማንሆል ክዳን ስራዎች እና ሌሎች ተያያዥ ስራዎችን በልዩ ሁኔታ አከናውኗል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.