የጎርፍ ስጋትን ለመከላከል የሚያስችሉ የድሬኔጅ ግንባታ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ
አዲስ አበባ፣የካቲት 4 ቀን 2016 ዓ.ም፡- በአዲስ አበባ ከተማ የጎርፍ ስጋትን ለመቀነስና ለመከላከል የሚያስችሉና ከ6.4 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው የድሬኔጅ መስመሮች በግንባታ ላይ ይገኛሉ፡፡
በአሁኑ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በበጋ የዝናብ ወቅትና በክረምት ጊዜ በተደጋጋሚ የጎርፍ ስጋት የሚያጋጥማቸው ቦታዎችን በጥናት በመለየት በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ የድሬኔጅ መስሮች ግንባታና የፅዳት ስራዎችን በስፋት እያከናወነ ይገኛል፡፡
አሁን ላይ በባለሥልጣኑ የራስ ኃይል እየተገነቡ ከሚገኙ የድሬኔጅ መስመሮች መካከል ገላን አካባቢ፣የካ አባዶ፣ አያት ዞን 8፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ ለቡ ሙዚቃ ሰፈር እና ሌሎችም አካባቢዎች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity