+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች የአክሰስ መንገድ ግንባታ በመከናወን ላይ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች እየገነባቸው ከሚገኙ የአስፋልት መንገዶች በተጨማሪ፣ የውስጥ ለውስጥ የጠጠር መንገዶችን በመገንባት የህብረተሰቡን የመግቢያና መውጫ መንገድ ችግር ለማቃለል በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የውስጥ ለውስጥ የጠጠር መቃረቢያ መንገድ ግንባታ እየተከናወነ ከሚገኝባቸው ሥፍራዎች መካከል በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች ይገኙበታል፡፡

ግንባታው ላይ 28 የስራ ተቋራጮች እየተሳተፉበት የሚገኝ ሲሆን፣ ጎንድዋና ኢንጂነሪንግ ደግሞ የማማከር ሥራውን እያከናወነ ይገኛል፡፡

ከ305 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየጠከናወነ የሚገኙት የውስጥ ለውስጥ የጠጠር መንገዶች ግንባታ በአጠቃላይ 29.55 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 10 ሜትር የጎን ስፋት አላቸው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.