ቋሚ ኮሚቴው የባለሥልጣኑን የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ገመገመ
የካቲት 1 ቀን 2016 ዓ.ም ፣ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የመሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱን የግማሽ በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ገምግሟል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ባለፉት ስድስት ወራት ያከናወናቸውን ስራዎች የሚያሳይ ሪፖርት የእቅድ በጀት እና ስትራቴጅክ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብነት ኤርገንዶ አቅርበዋል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ክንፈ አዲስ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ያከናወናቸው የመንገድ -መሰረተ ልማት ስራዎች በከተማዋ አይነተኛ ለውጥ ማሳየት የተቻለበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡ አክለውም መዲናዋ አሁንም ከሚያስፈልጋት የመንገድ ልማት ፍላጎት አንፃር ሰፊ ስራዎችን መስራት የሚጠይቅ በመሆኑ በባለስልጣኑ እየታየ ያለውን ውጤታማ የፕሮጀክት አፈፃፀም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የምህንድስና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ታከለ ሉለና በቋሚ ኮሚቴው አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ኢንጂነር ታከለ ከወሰን ማስከበር ጋር ተያይዞ እያጋጠመ ያለውን ተግዳሮት በመፍታት በኩል ቋሚ ኮሚቴው የሚያደርገውን ድጋፍና ክትትል አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity