+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በከተማዋ እየተገነቡ የሚገኙ የመንገድ ፕሮጀክቶች የትራፊክ ፍሰትንና ደህንነትን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ መሆናቸው ተገለፀ

አዲስአበባ፣ጥር 28 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች በከተማዋ የትራፊክ ፍሰትንና ደህንነትን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ግዙፍ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ላይ የተገኙት በትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን የመንገድ ትራፊክ ኢንጂነሪንግ ኦፕሬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ አልማዝ ማሞ በአሁኑ ወቅት በከተማዋ እየተገነቡ የሚገኙ ትላልቅ የመንገድ ፕሮጀክቶች የትራፊክ ፍሰትን እና ደህንነትን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

ወ/ሮ አልማዝ አክለውም በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች አማራጭና አቋራጭ መንገዶች መገንባት መቻላቸው የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎችን ከማሳደግ ጎን ለጎን ሊፈጠር የሚችለውን የትራፊክ መጨናነቅና ድንገተኛ አደጋ ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖራቸዋል ብለዋል፡፡

በባለሥልጣኑ የህዝብ ግንኙነትና የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ገነት ዲባባ በበኩላቸው ጉብኝቱ የመንገድ ፕሮጀክቶቹ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በኩል ከፍሰትና ከደህንነት አንፃር ሊሰሩ የሚገባቸውን የመሰረተ ልማት ስራዎች አስቀድሞ ለማቀድና ለማዘጋጀት እንደሚረዳቸው ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይም የሁለቱን ተቋማት ተናቦ የመስራት አቅምን ሊያሳድጉ የሚችሉ መሰል የጉብኝትና የውይይት መድረኮች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም ወ/ሮ ገነት ጨምረው ገልፀዋል፡፡

በትራፊክ ማኔጅመንት አመራሮች ከተጎበኙት የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል የለቡ ማሳለጫ ድልድይ፣ የቃሊቲ አደባባይ -ቱሉ ዲምቱ አደባባይ እና የቃሊቲ አደባባይ – ቡልቡላ ቂሊንጦ 2ኛ ቀለበት መንገድ አደባባይ ይገኙበታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.