+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የቃሊቲ – ቡልቡላ – ቅሊንጦ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ አሁናዊ ገፅታ

በቡልቡላና አቃቂ ወንዞች ላይ የተገነቡትን እና በድምሩ ግማሽ ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸውን ግዙፍ የወንዝ መሻገሪያ ድልድዮች አካቶ እየተገነባ የሚገኘው የቃሊቲ አደባባይ – ቡልቡላ – ቂሊንጦ አደባባይ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ የማጠቃለያ ምዕራፍ ላይ ደርሷል፡፡

በአሁኑ ወቅት በከፊል አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው ይህ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት፤ ወደ ቃሊቲ አደባባይ እና አቦ ቤተክርስቲያን መቃረቢያ ላይ የሚገኘው 160 ሜትር ርዝመት ያለው የመንገዱ ክፍል ላይ የሰብ ቤዝ እና የሙሌት ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

በደቡብ አዲስ አበባ ክፍል እየተገነባ የሚገኘው የቃሊቲ – ቡልቡላ – ቂሊንጦ የመንገድ ፕሮጀክት 10.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና ከ50 ሜትር የጎን ስፋት ያለው አዲስ የመንገድ ግንባታ ሲሆን፣ አሁን ላይ አጠቃላይ የፊዚካል አፈፃፀሙም ከ 91 በመቶ በላይ ደርሷል፡፡

ፕሮጀክቱ የከተማዋን የኢንዱስትሪ ፓርክ በመንገድ መሠረተ-ልማት የሚያስተሳስርና ከቱሉ ዲምቱ የክፍያ መንገድ አቅጣጫ ወደ ከተማዋ ለሚገቡና ለሚመጡ ተሸከርካሪዎች የወጪ ገቢ ኮሪዶር ሆኖ የሚያገለግል ዋና መንገድ በመሆኑ በቃሊቲ ቱሉ ዲምቱ መንገድ ላይ የሚኖረውን የትራፊክ ጫና እንደሚያቃልል ይታመናል፡፡

በተጨማሪም በኮዬ ፈቼ እና አካባቢው ባሉ የጋራ መኖሪያ መንደሮችና በዙሪያው ያሉ ነዋሪዎች በአቋራጭ ወደ መሃል ከተማ እንዲጓጓዙ የሚያስችል መንገድ በመሆኑ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ከፍ ያለ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.