+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራዎችን በተሻለ ጥራትና ቅልጥፍና ለማከናወን የሚያስችል አዲስ ማሽን አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ጥር 25 ቀን 2016 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከዚህ በፊት በከተማዋ የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራዎች ላይ ሲጠቀምባቸው ከነበሩ ማሽነሪዎች በዓይነቱ ልዩ የሆነ ሜካኒካል ሶይል ስታብላይዘር ማሽን ጥቅም ላይ ማዋል ጀመረ፡፡

በተቋሙ የመሳሪያዎች አቅርቦት ታሪክ የመጀመሪያ የሆነው ይህ የመንገድ ግንባታና ጥገና መሣሪያ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከጃፓን መንግስት ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በቅርቡ ወደ ሀገር ውስጥ የገባ ማሽን ነው፡፡

ከዚህ ቀደም በነበረው የአሰራር ሂደት አፈር ተቆርጦ በማውጣት በአዲስ ማቴሪያል የመተካት ስራ ይከናወን የነበረ ሲሆን፤ አሁን ላይ ወደ ሥራ የገባው ሜካኒካል የአፈር ማመቂያ ማሽን የቀድሞውን የአሰራር ሂደት በማስቀረት፣ በነባር መንገዶች ግንባታና ጥገና ስራ ላይ በየደረጃው የሚገኘውን የመንገዱን ክፍል ቆፍሮ ማውጣት ሳያስፈልግ ባለበት ሁኔታ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል ነው፡፡

አዲሱ ቴክኖሎጂ በመንገድ ግንባታና ጥገና ስራ ወቅት በአፈር ቆረጣና ማጓጓዝ ሥራ እንዲሁም በግንባታ ግብዓት አቅርቦትና በተሽከርካሪዎች ምልልስ የሚባክነውን ጊዜና ወጪ በመቆጠብ፣ በተሻለ ጥራትና በፍጥነት የመንገድ ግንባታና ጥገና ስራዎችን ለማከናወን እገዛ ያደርጋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.