ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከ515 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ልዩ ልዩ የግንባታ ግብዓቶች በማምረት ለአገልግሎት አብቅቷል
አዲስ አበባ፣ ጥር 21 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት ውስጥ ለመንገድ ግንባታና ጥገና አገልግሎት የሚውሉ ከ515.6 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ልዩ ልዩ የግብዓት ምርቶችን አምርቷል፡፡
ባለስልጣኑ ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ካመረታቸው የግንባታ ግብዓቶች መካከል 175.4 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ የካባ ምርቶች፣ 195.8 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው የሲሚንቶ ውጤቶች እና 144.4 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የአስፋልት ኮንክሪት ውጤቶችን በራስ አቅም በማምረት ለተለያዩ የግንባታና ጥገና ስራዎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ አድርጓል፡፡
ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የተለያዩ የግንባታ ግብዓቶችን በራስ አቅም ማምረት በመቻሉ የግንባታና የጥገና ስራዎች በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲከናወኑ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity