የቦሌ ኤርፖርት – ጎሮ የመንገድ ፕሮጀክት አሁናዊ የአፈፃፀም ሁኔታ
ከቦሌ ብራስ የቀለበት መንገድ መጋጠሚያ ተነስቶ፣ በቦሌ ኤርፖርት በኩል ወደ ጎሮ ቀለበት መንገድ የሚዘልቀው ይህ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በአጠቃላይ 4.9 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 60 ሜትር የጎን ስፋት ያለው አዲስ የመንገድ መዳረሻ ነው፡፡
የመንገድ ፕሮጀክቱ ከቱሉ ድምቱ የክፍያ መንገድ አቅጣጫ በጎሮ በኩል ወደ መሐል አዲስ አበባ የሚገቡና የሚወጡ ተሽከርካሪዎች የትራፊክ መጨናነቅ እንግልት ሳይገጥማቸው በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲጓዙ የሚያስችል ምቹ እና አቋራጭ መንገድ ነው፡፡
ይህ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት ከቦሌ ብራስ የቀለበት መንገድ መጋጠሚያ ጀምሮ 1.3 ኪሎ ሜትር የሚሆነው የመንገዱ ክፍል የመጀመሪያ ደረጃ አስፋልት ለብሶ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን፣ ከጉምሩክ ጀምሮ እስከ ውጨኛው የቀለበት መንገድ መጋጠሚያ ባለው ቀሪው የመንገዱ ክፍል ላይ ደግሞ የሙሌት፣ የቤዝ ኮርስ፣ ከርቭ ስቶን፣ የሰብ ቤዝ፣ የድልድይ፣ የከልቨርት ቦክስና የድጋፍ ግንብ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል፡፡
አሁን ላይ የፕሮጀክቱ አፈፃፀም 55.8 በመቶ የደረሰ ሲሆን በቅርብ ጊዜ ውስጥ የአስፋልት ማንጠፍ ስራ እንደሚጀመር ይጠበቃል፡፡
የቦሌ ኤርፖርት – ጎሮ የመንገድ ግንባታ ፕሮጄክት ከቦሌ ኤር ፖርት ከፍ ብሎ በስተግራ በኩል ከገርጂ ሮባ ዳቦ የመንገድ መረብ ጋር እንዲተሳሰር ተደርጎ እየተገነባ በመሆኑ በአካባቢው ያለውን የትራፊክ ፍሰት በማቀላጠፍ በኩል ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖረው ይታመናል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity