ባለፉት 6 ወራት በተሽከርካሪ ግጭት ምክንያት ከ4.8 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የመንገድ መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት ደርሷል
አዲስ አበባ ጥር 20 ቀን 2016 ዓ.ም፡- በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውስጥ በተሸከርካሪዎች ግጭት ሳቢያ 4.8 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ባለው የመንገድ መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡
ባለፉት 6 ወራት የደረሱ 181 የግጭት አደጋዎች በመንገድ ሀብት ላይ ጉዳት ያደረሱ ሲሆን፤ ከእነዚህ የግጭት አደጋዎች መካከል 59 አደጋዎች በቀለበት መንገድ ላይ፣ 122 ግጭቶች ደግሞ ከቀለበት መንገድ ውጪ የደረሱ ናቸው፡፡
በተሽከርካሪ ግጭት ሳቢያ ጉዳት ከደረሰባቸው የመንገድ ሀብቶች መካከል፤ የመንገድ መብራት ምሶሶዎች፣ የትራፊክ ምልክቶች፣ የአቅጣጫና ርቀት አመላካች ሰሌዳዎች፣ የእግረኛ መከላከያ አጥሮች፣ የመንገድ ማካፈያ ግንቦች እና የማንሆል ክዳኖች ይገኙበታል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity