+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ጀርመን አደባባይን በማንሳት በትራፊክ መብራት የመተካት ሥራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19 ቀን 2016 ዓ.ም፤ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ አደባባዮች ላይ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ለማቃለል የትራፊክ ፍሰት ማሻሻያ ሥራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ።

አሁን ላይ አደባባዮችን በማንሳት በትራፊክ መብራት የመቀየር ሥራ እየተከናወነባቸው ከሚገኙ አካባቢዎች መካከል ጀርመን አደባባይ አንዱ ነው፡፡

በዛሬው ዕለት የማሻሻያ ስራ የተጀመረበት ይህ አደባባይ ከኃይሌ ጋርመንት – መብራት፣ ከአየር ጤና፣ ከጎፋ እንዲሁም ሜክሲኮ ሳር ቤት የሚንቀሳቀሱ አሽከርከሪዎችን የሚያስተናግድ በመሆኑ የአደባባይ ማሻሻያ ስራ መከናወኑ በአካባቢው ያለውን ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰትና ጫና በአግባቡና በፍጥነት ለማስተናገድ የሚያግዝ ይሆናል፡፡

ባለሥልጣን መስሪያቤቱ የትራፊክ ፍሰት ማሻሻያ ስራውን የትራፊክ እንቅስቃሴ በማይበዛባቸው ክፍለ ጊዜያት በመስራት በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ሙሉ በሙሉ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ እየሰራ ይገኛል።

የመንገዱ ተጠቃሚዎችም የትራፊክ ፍሰት ማሻሻያ ሥራው እስኪጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ የበኩላቸውን አውንታዊ ድርሻ እንዲወጡ ባለሥልጣን መስሪያቤቱ ያሳስባል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.