+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ባሳለፍነው ሳምንት በተለያዩ አካባቢዎች የውሃ መፍሰሻ መስመሮች ክዳን ጥገና ስራ ተከናውኗል

ታህሳስ 23 ቀን 2016 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በስርቆትና በተሽከርካሪ ጉዳት ደርሶባቸው ክፍት የሆኑ የውሃ መፋሰሻ መስመር ክዳኖችን እየጠገነ ይገኛል፡፡

በከተማዋ የመንገድ ዳርቻዎች የተዘረጋውን የድሬኔጅ መስመር ተከትሎ የተገነቡት የኮንክሪት ማንሆል ክዳኖች በተሽከርካሪ ግጭት፣ በስርቆትና በተለያዩ ምክንያቶች ክፍት በመሆናቸው የዝናብ ውሃ መፋሰሻ መስመሮች አገልግሎት እንዲስተጓጎል እና የትራፊክ እንቅስቃሴውንም ለአደጋ ማጋለጡ ይታወሳል፡፡

ይህንን ችግር ለመፍታት አሁን ላይ ችግሩ በሚታይባቸው መንገዶች ላይ መጠነ ሰፊ የማንሆል ክዳኖች መልሶ የመተካት ሥራ እየተከናወነ ሲሆን፣ ባሳለፍነው ሳምንት የማንሆል ጥገና ስራ ከተደረገላቸው አካባቢዎች መካከል ከጎሮ – አይ.ሲ.ቲ አደባባይ፣ አያት 49 አካባቢ፣ መንዲዳ፣ ከሰሚት 72 – ንቡ ሚካኤል – ኖህ ሪል ስቴት፣ ኦሎምፒያ ደንበል አካባቢ፣ ከሳርቤት – ሜክሲኮ አካባቢዎች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

የማንሆል ክዳኖች በአግባቡ መከደናቸው የእግረኛ መንገዶች ለተጠቃሚዎች ምቹ እና ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ከማስቻላቸውም ባሻገር፣ የድሬኔጅ መስመሮች የዝናብ ውሃን በአግባቡ እንዲያስተናግዱ እና የከተማዋ መንገድ ውብና ጽዱ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው፡፡

በመሆኑም ሕብረተሰቡ የጋራ ሀብት የሆነውን የከተማዋን መንገድ በባለቤትነት ስሜት ከጉዳት እንዲጠብቅ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.