+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የፈፃሚዎችን የስራ ክህሎት የሚያጎለብት ስልጠና መሰጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 22 ቀን 2016 ዓ.ም፡- በከተማ ደረጃ እየተካሄደ ያለው የሠራተኞች የአቅም ግንባታ አካል የሆነው የስራ ክህሎት ስልጠና የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን መሰጠት ተጀመረ።

ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር የሚያካሂደው የሰራተኞችና የአመራሮች የስራ ክህሎት ስልጠና በተግባቦት ክህሎት፣ በሙያዊ ሥነ-ምግባር፣ በአገልግሎት አሰጣጥ እና ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው፡፡

የባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ የስልጠና ማዕከል ዳይሬክቶሬት ኃላፊ አቶ መስፍን ከበረ ስልጠናው የተግባቦት ክህሎትን ለመጨመር፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻልና ጥሩ የስራ ላይ ሥነ-ምግባር ለመላበስ የሚያስችል በመሆኑ የሰራተኞችን የመፈፀም አቅም ለማዳበር እንደሚያግዝ ገልፀዋል፡፡

አቶ መስፍን አያይዘውም ሰልጣኞች ከስልጠናው ያገኙትን ዕውቀት ወደ ተግባር በመቀየርና ውጤታማ የስራ አፈፃፀም በማስመዝገብ የተቋሙን ተልዕኮው በላቀደረጃማሳካትእንደሚጠበቅባቸው አስታውቀዋል፡፡

ስልጠናው ከታህሳስ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በአምስቱም የመንገድ ሀብት አስተዳደር ቅርንጫፎች፣ በሁሉም ሎቶች እና በዋናው መስሪያ ቤት ለሚገኙ የባሥልጣን መስሪያ ቤቱ ሰራተኞችና አመራሮች በተለያዩ ቀናት እንደሚሠጥ ከባለሥልጣኑ የስልጠና ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.