+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ለአደጋ ስጋት ምክንያት የሆኑ ችግሮችን ተቋማት ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር እንዲፈቱ የስራ መመሪያ ተሰጠ።

በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ ቤት አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ከተማ ተቆፍረዉ ክፍቱን በተተዉና ዉሀ ባቆሩ ጉድጓዶች ዉስጥ በሰዉ ህይወት ላይ እየደረሰ ያለዉን ጉዳት ለመከላከል የሚያስችል የምክክር መድረክ ከሚመለከታቸዉ ባለ ድርሻ አካላት ጋር ዛሬ ህዳር 25 ቀን 2016 ዓ.ም ተካሂዷል::

በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ክብርት ወ/ ሮ ሂክማ ከይረዲን በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት ጉዳዩ የሚመለከተን ተቋማት ሁሉ ተቀናጅተን በመስራት በሰዉ ህይወት ላይ እየደረሰ ያለዉን አደጋ ለመከላከል የሚያስችል አስቸኳይ መፍትሄ መስጠት አለብን ሲሉ በአጽንዖት ሰጥተዉ ተናግረዋል።

በከተማዉ ተቆፍረዉ ክፍት የተተዉና ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ጉድጓዶች እያደረሱ ያሉትን ጉዳትና የችግሩን አሳሳቢነት የሚያመለክት ጥናታዊ ሰነድ በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በኩል ቀርቧአል።

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍስሃ ጋር ደው በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት በየአንዳንዱ እንቅስቃሴና ስራዎች ሁሉ አደጋ መከላከል ላይ የቅድሚያ ትኩረት መሰጠት አለበት ካሉ በኋላ ኃላፊነትን በአግባቡ ባለመወጣት ለሚደርሰ አደጋ የተጠያቂነት አሰራር መስፈን እንዳለበት ተናግረዋል።

በዉይይት መድረኩ የተሳተፉ በለድርሻ አካላት በበኩላቸዉ እንደተናገሩት ለአደጋ የተጋለጡና በሰዉ ህይወት ላይ አደጋ እያደረሱ ያሉ ጉድጓዶች መኖራቸዉ እንደሚታወቅ ጠቅሰዉ ችግሩ ዘርፈ ብዙ በመሆኑ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ተቀናጅተዉ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚጠበቅባቸዉ ጠቅሰዉ ለዚህም የከተማ አስተዳደሩን ድጋፍ ጠይቀዋል።

ክብርት ወ/ሮ ሂክማ ኸይረዲን በማጠቃለያ ንግግራቸዉ እንዳሳሰቡት የዜጎችን ህይወት ከአደጋ ከመጠበቅ በላይ የሚቀድም ስራ የሌለን በመሆኑ ከጉዳዩ አሳሳቢነት አንጻር አስቸኳይ መፍትሄ ለመስጠት የሚያስችል ከሁሉም ተቋማት ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደስራ እንዲገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!

Comments are closed.