+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ቦሌ ሚካኤል አካባቢ የሚገኘው አደባባይ ተነስቶ ለትራፊክ ክፍት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ቦሌ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ በሚገኘው አደባባይ የሚታየውን የትራፊክ ፍስት የተቀላጠፈ ለማድረግ አደባባዩን የማንሳትና በትራፊክ መብራት የመተካት ሥራ ለማከናወን ካለፈው ማክሰኞ ምሽት ጀምሮ የመንገድ ሥራ መጀመሩ ይታወሳል።

አሁን ላይ የትራፊክ ፍሰት ማሻሻያ ስራው የትራፊክ እንቅስቃሴ በማይበዛባቸው የምሽት ክፍለ ጊዜና የዕረፍት ቀናትን በመጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ የአደባባይ ማንሳትና አስፋልት የማልበስ ሥራው ተገባዶ መንገዱ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

በአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ በኩል የሚከናወነውን የትራፊክ መብራት ተከላ ሥራን ጨምሮ ሌሎች ቀሪ የማጠናቀቂያ ስራዎች በአካባቢው በትራፊክ እንቅስቃሴ ላይ ተፅዕኖ በማያሳድር መልኩ በቀጣዮቹ ቀናት እንደሚከናወን ይጠበቃል።

የትራፊክ ፍሰት ማሻሻያ ስራው መከናወኑ ከቅሊንጦ – ቡልቡላ – ቦሌ ሚካኤል የመንገድ መረብ ጋር ተሳስሮ በአካባቢው እየጨመረ የመጣውን የትራፊክ መጨናነቅ በአግባቡና በፍጥነት ለማስተናገድ እንደሚያግዝ ይታመናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.