የከተማዋን የእግረኛ መንገዶች የማዘመን ስራ እየተከናወነ ይገኛል
አዲስ አበባ፣ ህዳር 23 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ በርካታ አካባቢዎች ላይ ምቹ እና ዘመናዊ የእግረኛ መንገዶችን እየገነባ ይገኛል፡፡
ባለስልጣን መስሪያቤቱ በአሁኑ ወቅት በከተማዋ አራቱም ማዕዘናት ለእግረኞች እንቅስቃሴ ምቹ ያልሆኑ ነባር የእግረኛ መንገዶችን መልሶ በመገንባት የማዘመን ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
አሁን ላይ የእግረኛ መንገድ መልሶ ግንባታ ስራ እየተከናወነላቸው ከሚገኙ አካባቢዎች መካከል ከሸበሌ ሆቴል- ሰንጋ ተራ ትራፊክ መብራት ድረስ በሁለቱም አቅጣጫ፣ ከጦር ኃይሎች አዋሽ ወይን ጠጅ ፋብሪካ፣ፒያሳ አደባባይ እና ፣ካሳንችስ አካባቢ ይገኙበታል፡፡
ባለስልጣን መስሪያቤቱ በከተማዋ በቅርቡ የሚካሄደው 37ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤና 43ኛው የስራ አፈፃፀሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ በስኬት እንዲጠናቀቅ ለማድረግ መንገዶችን ደማቅ ብርሀንና ልዩ ልዩ ህብረ ቀለማት ባላቸው መብራቶች የማስዋብና የማስጌጥ ፤ ልዩ ልዩ የመንገድ አካላትን የመጠገን እና የእግረኛ መንገዶችን የማዘመን ስራ በስፋት የሚያከናውን ይሆናል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity