ከስድስት ኪሎ ወደ ፈረንሳይ የሚወስደው የአስፋልት መንገድ በጥገና ላይ ነው
ህዳር 22 ቀን 2016 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከስድስት ኪሎ – ፈረንሳይ – ጉራራ ኪዳነምህረት የሚወስደውን መንገድ በመጠገን ላይ ነው፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች ለረጅም ጊዜ አገልግሎት በመስጠት የተጎዱና ለተሽከርካሪ እንቅስቃሴ አመቺ ያልሆኑ የአስፋልት መንገዶች በመጠገን የተሻለ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር እየሰራ ነው፡፡
የጥገና ስራ እየተከናወነለት የሚገኘው ከስድስት ኪሎ ፈረንሳይ – ጉራራ ኪዳነምህረት የሚወስደው መንገድ ከፍተኛ የትራፊክ እንቅስቃሴ የሚያስተናግድ በመሆኑ አልፎ አልፎ አስፋልቱ በመቦርቦሩ ለትራፊክ ፍሰት አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል፡፡
የጥገና ስራው 6 ኪ.ሜትር ርዝመት የሚሸፍን ሲሆን የተጎዳውን የአስፋልት ክፍል ቆርጦ በማንሳት እየተከናወነ ይገኛል፡፡
መንገዱ ደረጃውን ጠብቆ መጠገኑ በአካባቢው የሚኖረውን የትራፊክ እንቅስቃሴ ምቹ እና ደህንነቱ የጠበቀ እንዲሆን ያስችላል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity