+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ቃሊቲ ቆርኪ አካባቢ የውስጥ ለውስጥ መንገድ በመልሶ ግንባታ ደረጃ ጥገና እየተከናወነ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የህብረተሰቡን የመንገድ መሠረተ-ልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ እያከናወነ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ወቅት በመልሶ ግንባታ ደረጃ የውስጥ ለውስጥ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ስራ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች ውስጥ ቃሊቲ ቆርኪ አካባቢ የሚጠቀስ ነው፡፡

የመንገዱ አጠቃላይ ርዝመት 3.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 10 ሜትር የጎን ስፋት የሚሸፍን ሲሆን ከዚህ ውስጥ 1ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የመንገዱ ክፍል የጥገና ስራ እየተከናወነለት ይገኛል፡፡

የመንገድ ግንባታው መጠናቀቅ በአካባቢው ያለውን የመንገድ መሠረተ ልማት ችግር ከመቅረፍ ባለፈ በዋናነት በአካባቢው ለሚገኙ ኢንዱስትሪዎች፣ የመንግስት ተቋማት እና ለአካባቢው ነዋሪዎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በማሳደግ አስተዋፅዖ እንደሚያበረክት ይታመናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.