+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የነጭ ሪቫን ቀን ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 19 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ሠራተኞች በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለ32ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ18ኛ ጊዜ “መቼም፣ የትም፣ በምንም ሁኔታ ፆታዊ ጥቃትን ዝም አንበል!” በሚል መሪ ቃል የፀረ ፆታዊ ጥቃት ዘመቻ(የነጭ የሪቫን) ቀን አክብረዋል፡፡

በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ ቡድን መሪ ወይዘሪት ፀደንያ አበበ፤ ፆታዊ ጥቃት ሴቶችን ለአካለዊ፣ ለወሲባዊና ለስነልቦና ጥቃት የሚያጋልጥ የማህበረሰባዊ ችግሮች ዋነኛ አካል በመሆኑ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ፆታዊ ጥቃትን የመከላከል፣ የመቃወም እንዲሁም ጥቃት የደሰባቸውን ሰዎች ወደ ህግ አካላት በመውሰድ ፍትህ እንዲያገኙ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለበት ተናግረዋል።

የህብረተሰቡ ግማሽ አካል የሆኑት ሴቶች በማህበረሰብ እድገት ውስጥ የሚጠበቅባቸውን ገንቢ ሚና ለመወጣት አካላዊና ስነልቦናዊ ደህንነታቸው ሊጠበቅ እንደሚገባ የጠቆሙት ወይዘሪት ፀደንያ፣በሴቶች ላይ የሚፈፀመውን ፆታዊ ጥቃት ለመከላከል ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በጋራ ሊቆም እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በዕለቱ ከነጭ ሪቫን ቀን በተጨማሪ የዓለም አቀፍ የህፃናት ቀን፣ የአካል ጉዳተኞች ቀን፣ እንዲሁም የፀረ-ኤድስ ቀን በጥምረት ተከብሯል፡፡

በዝግጅቱ ላይ የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ምንነት፣ የጥቃት ዓይቶችና የሚያስከትሉት ጉዳትን በሚመለከት የተዘጋጀ ሰነድ ለተሣታፊዎች ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን፣ በበዓሉ ዙሪያ የተዘጋጀ ትምህርታዊ ተውኔት ለዝግጅቱ ታዳሚዎች ቀርቧል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.