+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በመንገድ ሀብት ላይ ህገ-ወጥ ተግባር በሚፈፅሙ አካላት ላይ የሚወሰደውየማስተካከያ እርምጃ እንደቀጠለ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በመንገድ መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት እያደረሱ በሚገኙ አካላት ላይ የእርምት እርምጃ በመውሰድ የመንገድ ሀብቱን ከጉዳት እየተከላከለ ይገኛል፡፡

ከተክለኃይማኖት ወደ ቀድሞው አትክልት ተራ በሚወስደው አስፋልትና እግረኛ መንገድ ላይ የግንባታ ግብዓት በማስቀመጥ መንገድ የዘጉ ግለሰቦች እንዲያነሱ የቃልና የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም ከድርጊታቸው ባለመቆጠባቸው፣ የባለስልጣኑ የማዕከላዊ አዲስ አበባ መንገድ ሀብት አስተዳደር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በመንገድ ወሰን ውስጥ የተከማቸው አሸዋና ጠጠር እንዲነሳ በማድረግ መንገዱን ለትራፊክ እንቅስቃሴ ክፍት አድርጓል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.