+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የአውጉስታ – ወይራ የመንገድ ፕሮጀክት ለትራፊክ እንቅስቃሴ ክፍት ተደርጓል

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 8 ቀን 2016 ዓ.ም፡- ከአውግስታ ወይራ ሰፈር አካባቢ ድረስ እየተገነባ የሚገኘው የመንገድ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ደረጃ የአስፋልት ማንጠፍ ስራው ተጠናቆ በከፊል ለትራፊክ እንቅስቃሴ ክፍት ተደርጓል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ 1.5 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ሲሆን በአቀጣይ አጭር ጊዜ ውስጥም የመጨረሻው የአስፋልት ንጣፍ ስራው ተጠናቆ ሙሉ ለሙሉ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ክፍት የሚደረግ ይሆናል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የእግረኛ መንገድ እና ተያያዥ ስራዎች እየተከናወኑ የሚገኝ ሲሆን አጠቃላይ የፕሮጀክቱ አፈፃፀምም ከ80 በመቶ በላይ ደርሷል፡፡

የመንገዱ ግንባታ ሲጠናቀቅ ከጦር ሀይሎች ወደ ቶታል በሚወስደው የውጪ ቀለበት መንገዱን በመያዝ በአውግስታ ወደ ቀኝ በመታጠፍ ወይራና ቤተል አደባባይ ለመሄድ አቋራጭ መንገድ በመሆን ያገለግላል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.