+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በሩብ ዓመቱ ከ308 ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ግንባታና የጥገና ስራዎች ተከናውነዋል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከ308 ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ግንባታና የጥገና ስራዎችን አከናውኗል፡፡

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሞገስ ጥበቡ በሩብ ዓመቱ ግንባታቸው የተጠናቀቀ 9 የመንገድ ፕሮጀክቶች የተመረቁበት እና የተቋሙን የመፈፀም አቅም የሚያሳድጉ በርካታ ማሽነሪዎች ወደ ስራ የገቡበት ወቅት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም እነዚህ ማሽነሪዎች ወደፊትም የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዘገብ አቅም የሚፈጥሩ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ኢንጅነር ሞገስ አያይዘውም የከተማዋን የትራፊክ እንቅስቃሴ ምቹ ለማድረግ፣ በተለያየ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን የአስፋልት መንገዶች መልሶ የመጠገን እና የተጀመሩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ በቀንና በሌሊት ክፍለ ጊዜ እየተካሄደ የሚገኘው የሥራ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.