+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የቃሊቲ አደባባይ – ቡልቡላ – ቅሊንጦ አደባባይ የመንገድ ግንባታ 89 በመቶ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 5 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በደቡባዊ አዲስ አበባ አቅጣጫ እያስገነባቸው ከሚገኙ የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው የቃሊቲ አደባባይ – ቡልቡላ – ቂሊንጦ አደባባይ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ 89 በመቶ ደርሷል፡፡

በወሰን ማስከበር ችግር ምክንያት የግንባታ ስራው ዘግይቶ የነበረውና ከቡልቡላ ወንዝ ወደ ቡልቡላ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የሚያገናኘው 1 ኪሎ ሜትር የሚሆነው የመንገዱ ክፍል አሁን ላይ የአስፋልት ማንጠፍ ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

ለዚህ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ተጨማሪ ድምቀት የሆኑት 2 ግዙፍ የወንዝ መሻገሪያ ድልድዮች ግንባታም በከፊል ተጠናቆ በአንድ አቅጣጫ ብቻ የትራፊክ አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው፡፡

ቀሪ የመንገድ ፕሮጀከቱን የግንባታ ስራዎች በአጭር ጊዜ ሙሉ በሙሉ አጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግም በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ በአካባቢው የሚገኘውን የቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክን በመንገድ መሠረተ-ልማት የሚያስተሳስርና ለከተማዋ ተጨማሪ የወጪ ገቢ ኮሪዶር ሆኖ ሊያገለግል የሚችል ዋና መንገድ በመሆኑ በቃሊቲ ቱሉ ዲምቱ መንገድ ላይ ሊፈጠር የሚችለውን የትራፊክ ጫና እንደሚያቃልለው ይታመናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.