+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ከአይሲቲ ፓርክ ወደ ጎሮ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ጥገና ተደረገለት

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1 ቀን 2016ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ የተለያዩ ማዕዘናት የመንገድ ጥገና ስራዎች እያከናወነ ይገኛል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በክረምት ወቅት በሚከሰት ጎርፍና በተለያዩ ምክንያች ብልሽት የገጠማቸውን መንገዶች በመለየት የጥገና ስራዎችን በማከናወን የከተማዋን የትራፊክ እንቅስቃሴ ምቹ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡

አሁን ላይ የጥገና ስራዎች እየተከናወነ ከሚገኙባቸው አካባቢዎች መካከል ከአይሲቲ ፓርክ ወደ ጎሮ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ተጠቃሽ ነው፡፡

የጥገና ስራው 2.4 ኪሎ ሜትር ርዝመት በ11 ሜትር የጎን ስፋት የሚሸፍን ሲሆን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የጥገና ስራው እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ከአይሲቲ ፓርክ ወደ ጎሮ አደባባይ የሚወስደው መንገድ የቱሉ ዲምቱ የፍጥነት መንገድን ከሰሜን ምስራቅ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ጋር በአጭር ርቀት የሚያገናኝ እና በየዕለቱ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ትራፊክ የሚያስተናግድ በመሆኑ የጥገና ስራው መከናወኑ በአካባቢው የነበረውን የትራፊክ እንቅስቃሴ የሚያሳልጥ ይሆናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.