በተለያዩ ምክንያቶች ለብልሽት የተጋለጡ መንገዶችን በመጠገን የተሻለ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር ለማስቻል እየተሰራ ነው
ጥቅምት 28 ቀን 2016 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ለረጅም ጊዜያት አገልግሎት በመስጠት የተጎዱና ለተሽከርካሪ እንቅስቃሴ አመቺ ያልነበሩ የአስፋልት መንገዶችን በተለያዩ አካባቢዎች እየጠገነ ይገኛል፡፡
ሰሞኑን የጥገና ስራ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል ቡልቡላ ከዩ.ኤን ፊልድ ሆስፒታል – ሪቬንቲ ማምረቻ ሳይት የሚወስደው የመንገድ ክፍል የሚጠቀስ ነው፡፡ የጥገና ስራው በመልሶ ግንባታ ደረጃ የተከናወነ ሲሆን በአጠቃላይ 350 ሜትር ርዝመት እና 8 ሜትር የጎን ስፋት የሚሸፍን ነው፡፡
በተመሳሳይም ከሳሪስ አቦ የመንገድ መጋጠሚያ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ላይ 110 ሜትር ርዝመት እና 12 ሜትር የጎን ስፋት ያለው የአስፋልት መንገድ ጥገና ስራው ተከናውኗል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity