+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የለቡ ትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድይ ግንባታ 80 በመቶ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25 ቀን 2016 ዓ.ም፡- በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ለቡ መብራት ኃይል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እየተገነባ የሚገኘው የለቡ ትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድይ ግንባታ 80 በመቶ አፈፃፀም ላይ ደርሷል፡፡

ቀደም ሲል 270 ሜትር ርዝመት ያለው የማሳለጫ ድልድዩ ስትራክቸር ግንባታ ተከናውኖ ለትራፊክ ክፍት መደረጉ የሚታወስ ሲሆን፣ አሁን ላይ የተሸጋጋሪ ድልድዩ ክፍል የመጀመሪያ ደረጃ የአስፋልት ንጣፍ ስራ ተጠናቆ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በመንገዱ የታችኛው ክፍል የማንሆል ግንባታ፣ የመቃረቢያ መንገዶች የድሬኔጅ መስመር ዝርጋታ፣ የሙሌት እና የሰብ ቤዝ ስራዎችም ተከናውነዋል፡፡

በቀጣይም ከለቡ ወደ ላፍቶ አቅጣጫ የሚወስደውን የመንገድ ፕሮጀክቱን ክፍል በአጭር ጊዜ የአስፋልት ማንጠፍ ስራ ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡

ይህ የመንገድ ፕሮጀክት የመቃረቢያ መንገዱን ጨምሮ አጠቃላይ 1.1 ኪ.ሜ ርዝመትና 40 ሜትር የሚደርስ የጎን ስፋት ያለው ሲሆን፣ የፕሮጄክቱ ግንባታ ሲጠናቀቅ አሁን ላይ በአካባቢው ያለውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ከመፍታቱም ባሻገር ለከተማዋ የገፅታ ተጨማሪ ውበት እንደሚያላብስ ይታመናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.