+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ወደ ኮልፌ የግብርና ምርት መሸጫ የገበያ ማዕከል የሚወስደው መንገድ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ከአንፎ – ቤተል የተገነባው እና ወደ ኮልፌ ግብርና ምርት መሸጫ የገበያ ማዕከል የሚወስደው መንገድ 520 ሜትር ርዝመትና 20 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን፣ መንገዱ ለአዲሱ የኮልፌ ቀራኒዮ የግብርና ምርቶች መሸጫ የገበያ ማዕከል የትራፊክ እንቅስቃሴ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ነው፡፡

ግንባታው በተጀመረ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት የበቃው ይህ ፕሮጀክት በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የራስ ኃይል የተገነባ ነው።

ከአምስቱ የከተማዋ የመግቢያ በሮች መካከል አንዱ ከሆነው የአምቦ የመንገድ ኔትወርክ ጋር የኮልፌ ግብርና ምርት መሸጫ የገበያ ማዕከልን የሚያስተሳስረው ይህ የመቃረቢያ መንገድ፣ ሸማቹን ህብረተሰብ ከአምራቹ ጋር በቀጥታ በማገናኝት በከተማችን የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት እየተደረገ ያለውን የገበያ ትስስር በማቀላጠፍ በኩል ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታል።

ከገበያ ማዕከሉ የመቃረቢያ መንገድ ግንባታ በተጨማሪ በ2.3 ሄክታር መሬት ላይ ባረፈው የገበያ ማዕከሉ ውስጥ በአንድ ጊዜ ከ200 በላይ ተሽከርካሪዎችን ማስቆም የሚችል ፓርኪንግ ተገንብቶለታል።

የገበያ ማዕከሉ በትላንትናው እለት በክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.