+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

ስልጠናው በተለያዩ የስራ መደቦችና ኃላፊነት ላይ ለሚገኙ 250 የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀናት የሚሰጥ ይሆናል፡፡

በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የስነ ምግባር መከታተያ የስራ ክፍል ኃላፊ ወ/ሮ ደመቀች መንገሻ ሙስና የሀገርን እድገት ወደ ኋላ የሚጎትት፣ የዜጎችን ሰርቶ የመለወጥ ተስፋ የሚያቀጭጭ እና በህዝብ የልማት ተጠቃሚነት ላይ ተፅእኖ የሚያሳድር ኢ-ሥነ ምግባራዊ ድርጊት በመሆኑ ሁሉም ህብረተሰብ አምርሮ ሊታገለው እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የተቀናጀ የፀረ ሙስና ስትራቴጂክ ሰነድ አዘጋጅቶ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን የገለፁት ወ/ሮ ደመቀች፣ በቀጣይም ተከታታይ የሆኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን በመስጠት ሙስናን የሚፀየፍ አመራርና ሠራተኛን ለማበራከት የሚሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ለሙስና በር የሚከፍቱ ተቋማዊ አሰራሮችን በየጊዜው በመፈተሽ የማስተካከያ እርምጃ ከመውሰድ ጎን ለጎን ግልፀኝነት እና ተጠያቂነትን ያሰፈነ የአሰራር ስርዓትን ይበልጥ አጠናክሮ ተግባራዊ በማድረግ የሙስና ተጋላጭነትን መቀነስ እንደሚገባ ወ/ሮ ደመቀች ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.