የፍል ውሃ – ሸራተን ሆቴል የአቋራጭ መንገድ ግንባታ በፍጥነት እየተከናወነ ይገኛል
አዲስ አበባ፡- ጥቅምት 12 ቀን 2016 ፣- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ የተለያዩ አከባቢዎች እየገነባቸው ከሚገኙ አቋራጭ የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው የፍል ውሃ – ሸራተን ሆቴል የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ በፍጥነት እየተከናወነ ይገኛል፡፡
ይህ የመንገድ ፕሮጀክት 450 ሜትር ርዝመት እና 40 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን በባለስልጣኑ የራስ ኃይል በመገንባት ላይ ነው፡፡ አሁን ላይ በመንገድ ፕሮጀክቱ የሰብ ቤዝ፣ የቤዝ ኮርስ፣ የከርቭ ስቶን፣ የእግረኛ እና ተያያዥ የግንባታ ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን፣ በአጭር ጊዜ ውስጥም አስፋልት የማንጠፍ ሥራ እንደሚከናወን ይጠበቃል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity