የአውጉስታ – ወይራ የመንገድ ፕሮጀክትን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 10 ቀን 2016 ዓ.ም፡- በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በተለምዶ አውግስታ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ጀምሮ እስከ ወይራ ድረስ እየተገነባ የሚገኘውን የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል፡፡
አሁን ላይ የመንገድ ፕሮጀክቱ ካለው አጠቃላይ 1.4 ኪ.ሜ ውስጥ 600 ሜትር የሚሆነው በመጀመሪያ ደረጃ የአስፋልት ንጣፍ የተከናወነለት ሲሆን ቀሪው የመንገዱ ክፍል ደግሞ የድጋፍ ግንብ፣ የከርቭ ስቶን፣ የሰብ ቤዝ እና የቤዝ ኮርስ ስራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡
በቀጣይ አጭር ጊዜ ውስጥም ሙሉ ለሙሉ አስፋልት ለማልበስ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ የሚገኙ ሲሆን አጠቃላይ የፕሮጀክቱ አፈፃፀምም ከ70 በመቶ ላይ ደርሷል፡፡
ይህን የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ቲኤን ቲ ኮንስትራክሽን /TNT construction / ከ308.3 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየገነባው የሚገኝ ሲሆን ኦሜጋ ኮንሰልቲንግ የተባለ አማካሪ ደርጅት ደግሞ የማማከር እና የቁጥጥሩን ስራ እየተከታተለው ነው፡፡
የመንገዱ ግንባታ ሲጠናቀቅ ከጦር ሀይሎች ወደ ቶታል በሚወስደው የውጪ ቀለበት መንገዱን በመያዝ በአውግስታ ወደ ቀኝ በመታጠፍ ወይራና ቤተል አደባባይ ለመሄድ አቋራጭ መንገድ በመሆን ያገለግላል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity