+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

“የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለሕብረብሐራዊ እንድነታችንና ሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው!” በሚል መሪ ቃል 16ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ

ጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አመራርና ሰራተኞች በአገር አቀፍ ደረጃ ለ16ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን በባለሥልጣን መስሪያቤቱ ዋናው ግቢ በጋራ አክብረዋል፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሞገስ ጥበቡ በመርሃ-ግብሩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ፤ ሰንደቅ ዓላማችን የሀገራችን የሉአላዊነት መገለጫ እና በህብረ – ብሔራዊነት ደምቀው በኢትዮጵያዊነት ማዕቀፍ በጋራ የቆሙ ህዝቦቿ የአብሮነት አርማ መሆኑን አውስተዋል፡፡

በጀግኖች ልጆቿ የዘመናት ተጋድሎ ፀንታና ተከብራ የኖረች ሀገራችን ኢትዮጵያን ለመጪው ትውልድ በክብርና በተሻለ የእድገት ደረጃ ለማሸጋገር፣ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በተሰለፈበት የሥራ መስክ ጠንክሮ መሥራትና ሀገራዊ አንድነትን የሚሸረሽሩ አፍራሽ ድርጊቶችን በጋራ መከላከል ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አመራርና ሠራተኞች ለሰንደቅ ዓላማችን እና ለሀገራችን ያለንን ክብር በተግባር ከምናረጋግጥባቸው መንገዶች አንዱ፣ በተሰማራንበት የመንገድ መሰረተ-ልማት መስክ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ተግተን በመሥራት በመሆኑ፣ ግንባር ቀደም የልማት አርበኝነታችንን ይበልጥ አጠናክረን ማስቀጠል ይኖርብናል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.