+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የሰሚት 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የአስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሥራ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23 ቀን 2016 ዓ.ም ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በራስ ኃይል ከሚገነባቸው የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው የሰሚት 40/60 የጋራ መኖርያ ቤቶች የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክት የግንባታ ስራ ተጠናቀቀ፡፡

ይህ የመንገድ ፕሮጀክት 1 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና ከ8 እስከ 15 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን፣ አሁን ላይ የእግረኛ መንገዱን ጨምሮ የግንባታ ስራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል፡፡

ባለሥልጣን መስሪያቤቱ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የነዋሪዎችን የመንገድ መሠረተ-ልማት ተጠቃሚነት ለማሳደግ በኮብል እና በአስፋልት ደረጃ በርካታ የመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

በጋራ መኖሪያ ቤቶች እየተገነባ የሚገኘው የመንገድ መሠረተ-ልማት፣ የቤት ልማት ተጠቃሚዎችን እንቅስቃሴ ምቹ ከማድረጉም በላይ ሌሎች የመሠረተ-ልማት አቅራቢ ተቋማትና አገልግሎት ሰጪዎች ለህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡

የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ የተካሄደበት ይህ ሥፍራ ከዚህ ቀደም ምንም ዓይነት የመንገድ መሰረት ልማት ያልነበረው ሲሆን፣ ግንባታው መካሄዱ የሰሚት 40/60 ኮንዶሚኒየም ነዋሪዎችን እና የአካባቢውን ማህበረሰብ የዕለት ዕለት እንቅስቃሴ በማሳለጥ ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት መፋጠን ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ይታመናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.