የኢሬቻ በዓልን በድምቀት ለማክበር የሚያስችሉ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች በመከናወን ላይ ናቸው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 23 ቀን 2016 ዓ.ም፡- በዚህ ሳምንት መጨረሻ አዲስ አበባ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል ቅድመ-ዝግጅት በበዓሉ ማክበሪያና እንግዶች በሚተላለፉባቸው ዋና ዋና መንገዶች ላይ ልዩ ልዩ የመንገድ ጥገና ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን እስከ አሁን ካከናወናቸው የመንገድ ዘርፍና ተያያዥ ስራዎች መካከል፤ በከተማዋ በሁሉም የመግቢያ በሮች አካባቢ የተቦሮቦሩ መንገዶችን የመጠገን፣ የመንገድ ዳር መብራቶችን ለማዘመን ከፍተኛ ብርሃን የሚፈነጥቁ ኤል.ኢ.ዲ አምፖሎችን የመቀየር እና የተቋረጡ የኤልክትሪክ መስመሮችን መልሶ የመዘርጋት ስራዎች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በዓሉ የሚከበርበትን አካባቢ የፅዳት፣ የመግቢያ እና የውስጥ ለውስጥ መተላለፊያ መንገዶችን ለእንቅስቃሴ ምቹ ለማድረግ የቤዝ ኮርስ መስተካከል ስራዎች ተሰርተዋል፡፡
በሌላም በኩል የአደጋ መከላከያ አጥሮች እና የድጋፍ ግንብ የቀለም ቅብ ሥራዎች እንድሁም በተለያዩ ምክንያቶች ጉዳት የደረሰባቸውን የማንሆል ክዳኖች የመቀየር እና መልሶ የመክደን ስራ በስፋት ተከናውኗል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
