+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የውስጠኛው ቀለበት መንገድ ክፍል የአስፋልት ጥገና ስራ እየተከናወነ ነው፡፡

መስከረም 21 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ፦ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያየ ምክንያት ጉዳት የደረሰበትን የውስጠኛውን የቀለበት መንገድ ክፍል እየጠገነ ይገኛል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች በዋና ዋና እና በአቋራጭ መንገዶች ላይ እያካሄዳቸው ከሚገኙ ልዩ ልዩ የመንገድ ጥገና ስራዎች በተጨማሪ፤ በምስራቅና በምዕራባዊው የውስጠኛው የቀለበት መንገድ ክፍል የተጎዱ ቦታዎችን በመለየት የአስፋልት ጥገና እያካሄደ ነው፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት የጥገና ስራ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል፤ ከቦሌ ሚካኤል – ቦሌ ኤርፖርት አደባባይ እና ከ18 ማዞሪያ – ጦር ኃይሎች የሚወስደው የቀለበት መንገድ ክፍል ይገኝበታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.