+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ባለሥልጣን መስሪያቤቱ በቅርቡ የተረከባቸውን አዳዲስ ማሽነሪዎች በመጠቀም የመንገድ ጥገና ሥራውን በማፋጠን ላይ ነው።

መስከረም 21 ቀን 2016 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም፣ በጠጣር ቆሻሻዎች ተደፍነው አገልግሎት መስጠት ያቆሙ የመንገድ ዳር ውሃ ፍሳሽ መተላለፊያ ቱቦዎችን በማፅዳት ላይ ይገኛል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በቅርቡ ከጃፓን መንግስት በተደረገ ድጋፍ ካገኛቸው በርካታ ማሽነሪዎች መካከል፣ የመንገድ ዳር የውሃ መተላለፊያ መስመሮችን በዘመናዊ መንገድ ማፅዳት የሚያስችል ቴክኖሎጂ የተገጠመላቸው ተሽከርካሪዎች ይገኙበታል፡፡

በደለልና በደረቅ ቆሻሻ የተደፈኑ ቱቦዎችን ለማፅዳትና ለመክፈት የሚያገለግሉት እነዚህ ማሽነሪዎች፣ ቀደም ሲል ጥቅም ላይ ይውል የነበረውን የሰው ጉልበት፣ ጊዜና ወጪን በመቀነስ፣ የድሬኔጅ መስመሮችን ደህንነት በፍጥነት ለመፈተሽና ለማስተካከል ከፍተኛ እገዛ በማበርከት ላይ ናቸው።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

Comments are closed.