+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በ2016 በጀት ዓመት 902 ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታና ጥገና ስራዎች ለማከናወን ታቅዷል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባስልጣን በ2016 በጀት ዓመት 902 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ልዩ ልዩ የመንገድ ግንባታና ጥገና ስራዎችን ለማከናወን በዕቅድ ይዟል፡፡

በበጀት ዓመቱ 31.62 ኪ.ሜ የአስፋልት፣ 22.39 ኪ.ሜ የጋራ መኖሪያ ቤቶች መንገድ፣ 49.19 ኪ.ሜ የጠጠር፣ 48.36 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገዶች መልሶ ግንባታ ለማከናወን ታቅዷል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ 95 ኪ.ሜ የኮብል ንጣፍ መንገዶች ግንባታ እና 1.88 ኪ.ሜ የድሬኔጅ መስመር ግንባታ የሚከናወን ሲሆን፣ በጠቃላይ በበጀት ዓመቱ 248.44 ኪ.ሜ የሚሸፍን የመንገድ ግንባታ ሥራዎች ለማከናወን ታቅዷል፡፡

በሌላም በኩል ባለስልጣኑ በተለያዩ ምክንያቶች ለብልሽት የተዳረጉ 102 ኪ.ሜ የአስፋልት፣ 35 ኪ.ሜ የጠጠር፣ 80 ኪ.ሜ የኮብል መንገዶች ጥገና ለማካሄድ ታቅዷል፡፡

ከአጠቃቀም ጉድለት በተደጋጋሚ ጉዳት እያጋጠማቸው የሚገኙትን የመንገድ ዳር የውሃ መፋሰሻ መስመሮች በመፈተሸ 349.36 ኪ.ሜ የድሬኔጅ መስመር ፅዳትና ጥገና እንዲሁም 13.5 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ጥገና ይከናወናል፡፡

የትራፊክ አደጋን ከመቀነስ አኳያ 65.92 ኪ.ሜ የሚሸፍን የነባርና የአዳዲስ መንገዶች የትራፊክ ቀለም ቅብ ስራ እና 8 ኪ.ሜ የእግረኛ መከላከያ አጥር ስራ፤ በድምሩ 654 ኪ.ሜ ልዩ ልዩ የመንገድ ጥገና ስራ በበጀት ዓመቱ ለማከናወን ታቅዷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በቁጥር 22 ድልድዮች እና 16 ሺህ የመንገድ ዳር መብራቶች ጥገና በዕቅዱ ከተካተቱ ዋና ዋና ተግባራት መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.