በመንገድ ሀብት ላይ ጉዳት በሚያደርሱ ህገ-ወጥ አካላት ላይ የእርምት እርምጃ እየተወሰደ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አባባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በመንገድ መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት እያደረሱ በሚገኙ ህገ-ወጦች ላይ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የእርምት እርምጃ እየወሰደ ይገኛል፡፡
የእግረኛ መተላለፊያ መንገዶችን ጨምሮ በተሸከርካሪ መተላለፊያ መንገዶች ላይ የግንባታ ቁሳቁስና ተረፈ ምርቶችን በማከማቸት የግንባታ ሥራ እያከናወኑ የሚገኙ አካላት ከህገ-ወጥ ድርጊታቸው እንዲታረሙ በተደጋጋሚ በቃልና በጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ቢሆንም ተፈፃሚ ባለማድረጋቸው በደቡብ፣ በምዕራብ እና በማዕከላዊ አዲስ አበባ የመንገድ ሀብት አስተዳደር ቅርንጫፎች በኩል የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ተደርጓል፡፡
በከተማዋ መንገዶች ላይ እየተካሄደ ያለው የግንባታ ቁሳቁስና ተረፈ ምርቶችን በማከማቸት፣ የተሸከርካሪ ጥገና፣ ህገ-ውጥ የንግድ እንቅስቃሴ እና ሌሎች በመንገድ ሃብት ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ተግባራት የዜጎችን በመንገድ ሃብት የመጠቀም መብት እየተጋፉና የከተማዋን ገፅታ እያበላሹ ይገኛሉ፡፡
ስለሆነም ባለሥልጣን መስሪያቤቱ በከተማዋ ደህንነቱ የተጠበቀ የመንገድ ሃብት እንዲኖር እና በከፍተኛ የመንግሥትና የህዝብ ሃብት የተገነቡ መንገዶች ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ ለማድረግ ከፀጥታ አካላትና ከሌሎች ባለድርሻዎች ጋር በመሆን የጀመረውን የእርምት እርምጃ በሁሉም የከተመዋ ክፍሎች አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
