የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ሠራተኞች የመፈፀም አቅምን የሚያሳድጉ አጫጭር ስልጠናዎች እየተሰጡ ነው
ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በበጀት ዓመቱ የዝግጅት ምዕራፍ ከሚያከናውናቸው አበይት ተግባራት መካከል አንዱ በሆነው የሠው ሃብት አቅም ግንባታ ስልጠና መስክ ለተቋሙ ተልዕኮ ስኬት የሚያግዙ አጫጭር ስልጠናዎችን ለሠራተኞቹ በተለያዩ መስኮች ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር እየሰጠ ይገኛል፡፡
በያዝነው ሳምንት ለባለሙያዎች እየተሰጡ ከሚገኙ ስልጠናዎች መካከል በኘሮትጀክት የጊዜ ሰሌዳ አዘገጃጀት ላይ ያተኮረው Primavera Project Planner P6 የሶፍት ዌር ሥልጠና ይገኝበታል፡፡
ለስድስት ተከታታይ ቀናት በሚዘልቀው በዚህ ስልጠና ላይ በምህንድስና ሙያ ዘርፍ እያገለገሉ የሚገኙ ሠራተኞች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
ስልጠናውን እየሰጡ የሚገኙት አቶ ማቲዎስ ፀጋዬ እንደጠቀሱት በመንገድ ኘሮጀክት ግንባታ ሂደት ከሚያጋጥሙ ችግሮች መካከል አንዱ የኘሮጀክት በተያዘለት ጊዜ አለመጠናቀቅ ተጠቃሽ መሆኑን ጠቁመው፤ የስልጠናው ዓላማም የኘሮጀክት የቆይታ ጊዜ እንዴት አንደሚሰላ እና እያንዳንዱ ኘሮጀክት ከተያዘለት የጊዜ ገደብ በላይ እንዳይዘገይ ሊወሰዱ በሚገባቸው አሰራሮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity