+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ምዘና ላይ ለተሳተፉ የኮሚቴ አባላት እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ ፣ነሐሴ 25 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የባለሥልጣን መስሪያቤቱ የ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ምዘና በተሣካ ሁኔታ መካሄዱ ተገለፀ

በምዘና ሥራው ላይ ለተሳተፉ የኮሚቴ አባላት እውቅና ተሰጠቷል፡፡

በእውቅና አሰጣጥ ሥነስርዓቱ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የተቋም ለውጥ፣ ድጋፍ ሰጪ ዘርፍ ስታፍ አሲስታንት አቶ አብደላ ረዲ እንደገለፁት ዓመታዊ የስራ አፈፃፀም ግምገማ መካሄዱ የተቋማትን የስራ አፈፃፀም ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍ ለማድረግ የሚረዳ እና የስራ ክፍሎች ከመረጃ አያያዝ እና ከዕቅድ አፈፃፀም አንፃር የሚታይባቸውን ክፍተት ፈጥነው በማረም በቀጣይ ተጠናክሮ ለመስራት የውድድር ስሜት እየፈጠረ መምጣቱን ጠቅሰው፣ ለምዘናው ሥራ መሳካት የበኩላቸውን ድርሻ ለተወጡ የሥራ መሪዎችና የባለሥልጣኑ ሰራተኞች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የተቋም አቅም ግንባታ ሲስተም ዲዛይን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አበዜ ሱለይማን በበኩላቸው፤ በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ዓመታዊ የስራ አፈፃፀም ምዘና ዘንድሮ ለስድስተኛ ጊዜ መከናወኑን ጠቁመው፣ ምዘናው የተቋሙን ዐብይ ተልኮ ውጤታማ ለማድረግ እና አገልግሎት አሰጣጡን የተሻለ ለማድረግ የሚያግዝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ወ/ሮ አበዜ አያይዘውም ምዘናው በአጠቃላይ በ5 ዘርፎች፣ በ39 የስራ ክፍሎች፣ በ4 አማካሪዎች እና በ87 ቡድኖች የተካሄደ መሆኑን ጠቅሰው፣ ሁሉም የስራ ክፍሎች በተዘጋጀው ስኮር ካርድ፣ እቅድ እና ሪፖርት መሰረት የተደራጀ የመረጃ አያያዝ ስርዓት እንዲኖር የሚረዳ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በምዘና ስራው ላይ ለተሳተፉ 30 የኮሚቴ አባላት እውቅና የሰጠ ሲሆን፣ ይህም የምዘና ስርዓቱ ቀጣይነት እንዲኖረው እንደሚያግዝ ዳይሬክተሯ አክለው ገልፀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.