ለትራፊክ እንቅስቃሴ አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች የመንገድ ጥገና ስራ እየተከናወነ ነው
ነሐሴ 27 ቀን 2015 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያዩ ምክንያቶች ጉዳት የደረሰባቸውን ዋና ዋና እና አቋራጭ መንገዶችን በመጠገን ለትራፊክ ፍሰት ምቹ እያደረገ ይገኛል፡፡
በክረምት ወቅት በመቦርቦራቸው ምክንያት ለትራፊክ እንቅስቃሴ አዳጋች የሆኑ መንገዶችን በአስፋልት ኮንክሪት በመጠገን መፍትሄ ከተሰጣቸው አካባቢዎች መካከል ሳርቤት አደባባይ፣ አራት ኪሎ፣ ከኤሊያና ሆቴል – አራዳ፣ ከዮሐንስ – ራስ ደስታ ያሉት የመንገድ ክፍሎች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
