በአዳዲስ የመኖሪያ አካባቢዎች በጠጠር ደረጃ የመዳረሻ መንገዶች እየተገነቡ ነው
ነሐሴ 22 ቀን 2015 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፦ በአዲስ አበባ ከተማ የመንገድ መሰረተ-ልማት ተደራሽነትን ለማሳደግ በአዳዲስ የመኖሪያ አካባቢዎች በጠጠር ደረጃ የመዳረሻ መንገዶች በመገንባት ላይ ናቸው።
አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የከተማዋን የመንገድ ኔትወርክ ይበልጥ በማስተሳሰር ደህንነቱ የተጠበቀ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር ለማስቻል ከሚያካሂደው መጠነ ሰፊ የመንገድ መሰረተ-ልማት ግንባታና ጥገና ሥራ ጎን ለጎን፤ የመንገድ መሠረተ ልማትን በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ አዳዲስ መንደሮች በተገነቡባቸው አካባቢዎች በጠጠር ደረጃ የመዳረሻ መንገዶች በመገንባት ላይ ይገኛል።
አሁን ላይ በጠጠር ደረጃ የመዳረሻ መንገድ እየተገነባባቸው ከሚገኙ አካባቢዎች መካከል ከናሆም አደባባይ – ገልማ አባገዳ ፣ ከናሆም አደባባይ – ሃና ማርያም መውጫ፣ ላምበረት አካባቢ እንዲሁም ከሲ.ኤም.ሲ – የተባበሩት አካባቢ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity