አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በመንገድ ጥገና መስክ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በመንገድ ጥገና መስክ ከሚያከናውናቸው ልዩ ልዩ ተግባራት የመንገድ ጠርዝና አካፋይ፣ እንዲሁም የእግረኛ መከላከያ አጥር ጥገና እና ቀለም ቅብ ሥራዎች ይገኙበታል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የከተማዋን የትራፊክ እንቅስቃሴ ምቹ ለማድረግ ባለፉት 12 ወራት ከአምስት ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት የሚሸፍን የእግረኛ መከላከያ አጥር ጥገና እና 178 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የቀለም ቅብ ስራ አከናውኗል፡፡
በመንገድ ጥገና መስክ እየተከናወነ የሚገኘው የመንገድ ጠርዝና አካፋይ የቀለም ቅብ ሥራ የትራፊክ አደጋ እንዲቀንስ ከሚኖረው አስተዋፅኦ ባሻገር ለከተማዋ ጎዳናዎች ተጨማሪ ውበት የሚያጎናፅፍ ነው፡፡
የመንገድ ሀብታችንን በጋራ እንጠብቅ!
ሰናይ ቀን!
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity