+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የሰራተኞችን የመፈፀም አቅም የሚያዳብሩ ተከታታይ ስልጠናዎች እየተሰጡ ይገኛሉ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 12 ቀን 2015ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያዩ የስራ መስክ ያሰማራቸውን ሰራተኞች የመፈፀም አቅም የሚያሳድጉ ተከታታይ ስልጠናዎች እየሰጠ ይገኛል፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የስልጠና ማዕከል ዳይሬክቶሬት ከኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲቱዩት ጋር በመተባበር የግንባታ ወጪ ግምት እና በጀት ዝግጅት (construction cost estimation and budgeting) በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከተለያዩ የስራ ክፍሎች ለተውጣጡ 70 ለሚሆኑ አመራር እና ባለሞያዎች ለሁለት ተከታታይ ቀናት ስልጠና ተሰቷል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት ከኮንስትራክሽ ማኔጅመንት ኢንስቲቱዩት ኢንጂነር ታምሩ መንግስት እንደገለፁት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በተያዘለት ጊዜ እና በጀት ለማጠናቀቅ እንዲሁም አፈፃፀማቸውን ለመገምገም መሰል የመፈፀም አቅም የሚያዳብሩ ስልጠናዎች መሰጠታቸው ፋይዳው ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

ኢንጂነር ታምሩ አያይዘውም የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ግምገማ ፣ የበጀት አጠቃቀም እና የግንባታ ወጪ ግምት ማዋጣት ላይ ግንዛቤ ከማስጨበጥ በተጨማሪ ዓለም አቀፍ ልምድ፣ እውቀቶችን እና ቴክኖሎጂዎች ጋር በማስተዋወቅ ጭምር ስልጠናው እንደተሰጠ ገልፀዋል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሠራተኛውን እውቀት፣ አመለካከትና ክህሎትን ሊያሳድጉ የሚችሉ ተከታታይ ስልጠናዎችን በመስጠት የተቋሙን የመፈፀም አቅም ለማሻሻል እየሰራ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.