+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የባለሥልጣኑ አመራርና ሰራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄዱ

ነሐሴ 11 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን አመራርና ሰራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች በአምስት መድረኮች ባካሄዱት ውይይት በአሁኑ ወቅት በተለይም በአማራ ክልል የተፈጠረውን የሰላም መደፍረስና ተያያዥ ችግሮች ለመፍታት በፌዴራልና በክልሉ መንግስት እየተወሰዱ ባሉ እርምጃዎች ላይ ውይይት አካሂደዋል።

በየመድረኮቹ የውይይት መነሻ ሃሳብ በአወያዮች የቀረበ ሲሆን፣ የክልሉ ህዝብ ለውጡ እውን እንዲሆን የነበረውን ሚና እና ህዝቡ በየጊዜው ያነሳቸው የነበሩ የሠላም፣ የዴሞክራሲና የልማት ጥያቄዎችን እንዲሁም በመንግስት በኩል ጥያቄዎቹን ለመፍታት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች እና ችግሮቹ በዘላቂነት የሚፈቱባቸው መንገዶች በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የውይይቱ ተሣታፊዎች እንደገለፁት የክልሉም ሆነ የሀገራችን ህዝብ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥያቄዎች ዘላቂ ምላሽ የሚያገኙት በውይይትና በሠላማዊ መንገድ ብቻ መሆኑን በመገንዘብ የታጠቁ ኃይሎች የህብረተሰቡን ሠላማዊ ኑሮ ከሚያውኩ እንቅስቃሴዎች እንዲታቀቡ በአፅንዖት አሳስበዋል።

መንግስትም በክልሉ ለዓመታት የተሻገሩ፣ ያልተፈቱ ችግሮችን ቅደም ተከተል በማስቀመጥ ከህብረተሰቡ ጋር በውይይት ለመፍታት የጀመረውን እንቅስቃሴ ይበልጥ አጠናክሮ እንዲቀጥል በአስተያየት ሰጪዎቹ ጠይቀዋል።

በአማራ ክልልም ሆነ በየትኛው የሀገራችን ክፍሎች ሠላም ያስፈልገናል ያሉት የውይይቱ ተሣታፊዎች፣ ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት በተጨባጭ እንዲረጋገጥ እንደ ዜጋ ሚናችንን እንወጣለን ሲሉ ለሠላምና ለአንድነት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.